ይህ አፕሊኬሽን ከ 100 በላይ ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱሳን መላእክትን ፣ ቅዱሳን አባቶችን ፤ ቅዱሳን እናቶችን እንዲሁም የልዑል እግዚአብሔርን ቅዱሳን ስእላትን ይዞዎል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚከበሩ አመታዊ እና ወርሃዊ በአላትን አካቶዋል ፤ በመጨረሻም ይህ አፕሊኬሽን መፅሃፍ ቅዱሳዊ ስሞችን ከነ ትርጉማቸው ይዞዋል፡፡
ቅዱሳን ስእላቱ የተሰበሰቡት፡
- ሊሸጡ የተዘጋጁ ቅዱሳን ስእላትን ፎቶ በማንሳት
- በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ የተሳሉትነ ስእላት ፎቶ በማንሳት
- ከተለያዩ ቅዱሳን አዋልድ መፃህፍት ላይ ያሉ ቅዱሳን ስእላትን ፎቶ በማንሳት
- እንዱሁም ከኢንተርኔት ላይ በመውሰድ ነው
ማስተዋል ያለብን ነገር ግን በዚህ አፕሊኬሽን ውስጥ የተካተቱት የተወሰኑት ቅዱሳን ስእላት ብቻ ናቸው፡፡ እጅግ ብዙ ያልተካተቱ አሉ፡፡