በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!
ስንክሳር ማለት የእግዚአብሔርን ረድኤት አጋዥ በማድረግ በበጎ ስጦታውም የተሰበሰበ ማለት ነው።
ይህ ሃይማኖቶታቸው የቀና የከበሩ አባቶች ፣ ከቅዱሳን ሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከነቢያት ፣ ከሐዋርያት ፣ ከሊቃነ ጳጳሳት ከኤጲስቆጶሳት ፣ ከመነኮሳትም ከመነኮሳትም ሁሉ ከገዳማውያንም ከገድሎቻቸው ከመላእከት አለቆችም ከድርሳናቸው የሰበሰቡትና ያቀነባበሩት አምላክን የወለደች እመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም ከአደረገቻቸው ድንቆች ተአምራቶችም የክብር ባለቤት የሆነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበዓላቶቹን መታሰቢያ በዘመናት ሁሉ እስከ ዓመቱ ፍፃሜ ሁል ጊዜ ምእመናን እንዲያነቡት እንዲሰሙትም ይሆን ዘንድ ተዘጋጀ።
ይህንንም ቅዱስ መጽሐፍ ሰብስበው ያቀነባበሩት በሽህ ሦስት መቶ ንጹሐን በሆኑ ሰማዕታት ዘመን ነው። የእሊህ የተባረኩ አባቶቻችን ጸሎታቸውና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኑር።
ለዘላለሙ አሜን !!
የቅዱሳንን ታሪክ ለማንበብ ከታሪካቸውም ለመማር እኛም በክርስትና ህይወታችን እንዲሁም በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያችን ውስጥ በዋነኝነት ቅዱሳኑ እንዲራዱን በሌላም መልኩ ከነሱ ከነሱ የክርስትና ህይወት በመነሳት እኛስ ምን ማረግ እንችላለን ከቅዱሳኑ ታሪክ ምንን እማራለው የሚለውን እንድናስብ ይረዳናል ብሎ በማሰብ እንዲሁም በብዙ መፅሃፈ ስንክሳርን ማግኘት በማይችሉ ምእመናን ጥያቄ መሰረት ይህን የሞባይል እንዲሁም ከጉዋደኞቾ ፣ ቤተሰቦቾ ፣ የስራ ባልደረቦቾ ባጠቃላይ ከወዳጅ ዘመዶቾ ጋር በመሆን ይጠቀሙበት ዘንድ ትልቁን የቤተክርስቲያን መፅሃፍ መፅሃፈ ስንክሳርን ጠቅለንም ባይሆን ፈጣሪ በፈቀደ የቻልነውን ሙሉውን ታሪክ ያልቻልነውን ደግሞ ዋና ታሪኩን ታሪኩን ጨምቀን አቅርበናል።
እርሶም እኝህን መንፈሳዊ ታሮኮች ሰአት መድበው በቀን ቢያንስ ከ3—10 ደቂቃ ወስደው የእለቱን ስንክሳር እንዲያነቡ እንዲማሩበት ከወዳጆቾ ጋርም ውይይቶችን እኒዲያረጉበት እንመክራለን።
በዚህ አፕሊኬሽን ውስጥ የተካተቱት ብዙሃኑ ቅዱሳን ከ 6 ቱ እህታማማች ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አብያተ ክርስትያናት ናቸው
እነዚህም አብያተ-ክርስትያናት: -
- የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
- የ ግብፅ / አሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
- የ ሶሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
- የ አርመንያ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
- የ ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
- የ ህንድ - ማንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ያንብቡ ያነበቡትንም ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመሆን ይወያዩበት - አፕሊኬሽኑንም ለሌላቸው ያካፍሉዋቸው
ድጋፍዎ አስተያየትዎ አይለየን
ፈጣሪ ከቅዱሳኑ ይደምረን
አሜን !!
በዚህ እለት ማን ቅዱስ እንደሚከብር ያውቃሉ? ከነ ታሪካቸው ገብተው ይመልከቱ ከበረከታቸውም ተካፋይ ይሁኑ። ይህንንም ስራ ሰርቶ ለማጠናቀቅ አመታትን የፈጀ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ አብዛኞቹን ፅሁፎቹን በማዘጋጀት የላቀ ሚና ለተገበረው ለዲ / ን ዮርዳኖስ አበበ ምስጋናችን ከልብ ነው።
ዲ / ን ዮርዳኖስም ለብዙ አመታት እድሜውን ሙሉ መንፈስ ቅዱስ ባቀበለው መጠን ጎንደር በሚገኘዉ በዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ የቅዱሳን ታሪክ በመማር ፣ በማንበብ ፣ በመተርጎም ፣ በመፃፍ ፣ በማዘጋጀት እና በማስተማር ጭምር የኖረ የቤተክርስቲያናችን የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ ነው። ይህንንም እርሱ ያዘጋጃቸውን ፅሁፎች በነፃ ምዕመንን ለማስተማር በፌስ ቡክ ፣ በቴሌ ግራም እንዲሁም ለኛም በነፃ ሰጥቶን እኛም ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማስተማር እና የቅዱሳን በረከትንም ለኛም ላንባቢውም እንድንካፈል በአፕሊኬሽን በአፕሊኬሽን መልክ አቅርበናል።
ስንክሳር * Sinksar - (Lives of Saints) á amharíska og enska.
ስንክሳር (የቅዱሳን ታሪክ) ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Sinksar (Synaxarium) rétttrúnaðar Tewahedo kirkjan
Í nafni föðurins, sonarins og heilags anda, einn Guð amen!
Til þess að læra af Synaxarium eða sögu og lífi kristinna dýrlinga og til að verða betri í kristni þinni, sérstaklega í rétttrúnaðar Tewahedo kirkjulífi, mælum við eindregið með að þú lesir bókina og fyrir þá sem ekki höfðu aðgang að bókinni hér er app fyrir það sem inniheldur helstu sögur með myndum sem sýna söguna.
Flestir dýrlinganna eru frá austurlensku rétttrúnaðarkirkjunni.
Þetta austurríska rétttrúnaðarsamfélag samanstendur af sex sjálfkirkjukirkjum:
- Eþíópíu rétttrúnaðarkirkjuna Tewahedo,
- Koptíska rétttrúnaðarkirkjan í Alexandríu,
- Sýrlensku rétttrúnaðarkirkjuna í Antíokkíu,
- Armeníska postulakirkjan,
- Erítreysku rétttrúnaðar Tewahedo kirkjuna, og
- Malankara rétttrúnaðarsýrlensku kirkjuna.
- Á amharísku og ensku.
Haltu áfram að lesa, ræðið það sem þú hefur lesið með öðrum kristnum mönnum og haltu áfram að deila appinu fyrir alla kristna heiminn.