ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

3,4
70 anmeldelser
10k+
Nedlastinger
Egnethet
Alle
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump

Om denne appen

«ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ» በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ዶግማ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ከ፲፪ መጻሕፍት በላይ ተካተውበት የቀረበ የመጻሕፍት መድብል ነው።
ይህ የመጻሕፍት መድብል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትርጓሜ ሊቃውንት የተራቀቁባቸውን እና የተጠበቡባቸውን ሲወርዱ ሲወራረዱ ለእኛ የደረሱ የትርጓሜ መጻሕፍት የተካተቱበት ነው። በሦስት ዐበይት ክፍሎች የተመደቡ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ያካተተው ይህ መድብል ምክርና ተግሳጽንም የያዘ ስለሆነ ብዙዎች እንደሚወዱት ተስፋ እናደርጋለን። በአዘጋጁ ታትመው የቀረቡና እና ለኅትመት ዝግጁ የሆኑ መጻሕፍትም የተካተቱበት ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል። በአዘጋጁ ከቀረቡ መጻሕፍት መካከል በቅብዐት ምንፍቅና አማኞች ለተጻፉ መጻሕፍት ተገቢ ምላሽ የተሰጠባቸውን «ደብረ አሚን - የሃይማኖት ተራራ» እና «ፍኖተ ጽድቅ - የእውነት ጎዳና» አካተናል። ከዚህ በተጨማሪም አዘጋጁ የጻፋቸው የተለያዩ ወጎች ፣ ትምህርቶችና ግጥሞችም ምክርና ተግሳጽን በስፋት አካተው ቀርበውበታል። ከእግዚአብሔር ለምን እንርቃለን? እግዚአብሔርስ ከእኛ ለምን ይርቃል? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመልስ እና ወደ ንስሐ የሚመራ «ለምን ርቀህ ቆምህ?» የተሰኘው የአዘጋጁ መጽሐፍም በዚሁ መድብል ውስጥ የተካተተ ነው። እነዚህ የአዘጋጁ መጻሕፍት ገበያ ላይ የማይገኙ መሆናቸው ይህን መተግበሪያ ልዩ ያደርገዋል።
ይህ መተግበሪያ በተጨማሪነት ቤተ ክርስቲያናችን ከዓመት እስከ ዓመት የምትገለገልባቸውን ድንቅ መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውንና መጽሐፈ ስንክሳርን ያካተተ ነው።
ይህ መተግበሪያ የያዛቸው መጻሕፍት ዝርዝር

፩. የአንድምታ ትርጓሜ ክፍል
- የጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ።
-የውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።
- የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።
- የአራቱ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ።

፪. የአዘጋጁ መጻሕፍት ክፍል
- ደብረ አሚን
- ፍኖተ ጽድቅ
- ለምን ርቀህ ቆምህ?
- አማኞችን ማጽናትና ማበርታት
- ወጎች
- ትምህርቶች
- ግጥሞች

፫. ሌሎች መጻሕፍት ክፍል።
- ሃይማኖተ አበው
- መጽሐፈ ስንክሳር
- ፍኖተ እግዚአብሔር
Oppdatert
31. okt. 2020

Datasikkerhet

Sikkerhet starter med en forståelse av hvordan utviklere samler inn og deler dataene dine. Fremgangsmåtene for personvern og datasikkerhet kan variere basert på bruk, region og alder. Utvikleren har oppgitt denne informasjonen og kan oppdatere den over tid.
Ingen data deles med tredjeparter
Finn ut mer om hvordan utviklere deklarerer deling
Ingen data samles inn
Finn ut mer om hvordan utviklere deklarerer innsamling
Dataene krypteres ved overføring
Dataene kan ikke slettes

Nyheter

Target API 29 (Android 10) updated