Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት

Inneholder annonser
4,5
554 anmeldelser
50k+
Nedlastinger
Egnethet
Alle
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump
Skjermdump

Om denne appen

Denne appen inneholder mer enn 400 forskjellige hellige bilder av etiopiske ortodokse Tewahedo-kirker, hellige hellige, hellige engler, hellige fedre, hellige mødre og hellige bilder av Gud med en liste over årlige, månedlige hellige dager som feires i den ortodokse Tewahedo-kirken og til slutt den app inneholder en liste over bibelske navn og hjernehinnene deres.

Vær oppmerksom på at de hellige bildene som finnes i denne appen ikke er de eneste det er mange hellige som ikke er inkludert i denne appen.

በዚህ መተግበሪያ ውስጥ ከ 400 በላይ የቅዱሳን ስዕላትን በማንኛውም ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ ካለ ኢንተርኔት እንዲሰራ በመተግበሪያው ውስጥ ስእላቱ እንዲካተቱ ተደርጎዋል ፡፡
ከቅዱሳኑ በረከት ረድኤት ይደርብን
አሜን !!!

ከዚህ በታች ያለው አቡነ ገብርኤል በ 1990 ካሳተሙት “ክብረ ቅዱሳን» ከሚለው መጻሕፍ የተወሰደ ነው

የጥንቱና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተል ክርስቲያን ሁሉ ከቅዱሳት ሥዕሎች ሁለት ዐበይት ጥቅሞችን ያገኛል ይኽውም ትምህርትና ረድኤት ናቸው። ይልቁንም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረው ቃለ እግዚአብሔር (አካላዊ ቃል) በኋለኛው ዘመን ሰውን ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ ከሥጋዋ ሥጋን ፣ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ ከኃጢአት ብቻ በቀር ፍጹም ሰው ሆኖ በድንግልና የተወለደውና ተሰቅሎ በሞቱ ዓለሙን ማዳኑን በሥዕል ገልጾ ማቅረብ መስበክ ፤ ማስተማር ነው። በዚህም መሠረት የጌታችንን የልደቱን ታሪክ ፣ የጥምቀቱን ታሪክ ፣ የስቅለቱን ታሪክ ፣ የትንሣኤውንና የዕርገቱን ታሪክ በሥዕል ነድፎ ለምእመናን ማቅረብ ማለት የጌታችንን ወንጌለ መንግሥት መስበክና ማስተማር ማለት ነው ምክንያቱም ሥዕል ራሱበጉልህ የተጻፈ ጽሑፍ ማለት ነውና። ጌታችን ተወለደ ፣ ተጠመቀ ፣ ተሰቀለ ፣ ሞተ ፣ ከሙታን ተለይቶተነሣ… የሚለው የወንጌሉ ታሪክ በሥዕል ማቅረብ ማለት ታሪኩን በጉልህ ጽፎ ማቅረብ ማለት ነው።
ሐዋርያው ​​ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ተግሳጽ ሲጽፍ «የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ ፤ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር »ያለው ኢየሱስና ታሪኩን በሚገባ አውቀውትና ከልብም ተረድተውት እንደ ነበር ለመግለጽ ነው (ገላ .3 ፤ 1-2)

ስለዚህ ከላይ እንደተገለጸው ቅዱሳት ሥዕሎች በመመልከትና ልብ ብሎ በማንበብ (በማስተዋል) ታሪኩን በሚገባ ማወቅና መረዳት ስለሚቻል ፤ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሥዕሎች የክርስትና ሃይማኖት አስተማሪዎችና አስረጂዎች መሆናቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው።

ሁለተኛው ጥቅም ከቅዱሳት ሥዕሎች የሚገኘው ሌላው ዐቢይ ጥቅም ደግሞ ረድኤት (ርዳታ) ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረበት በጣም ቅርብ የነበሩት የጥንት ክርስቲያኖች በጌታችን ሥዕል ፣ በቅድስት ድንግል ሥዕልና በቅዱሳን ሥዕሎች ይማፀኑ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል። በዘመናችን ተቆፍረው የተገኙ የጥንት አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሶችም በሥዕላተ ቅዱሳን መማፀን ጥንታዊ ትውፊት (ሥርዓት) እንደሆነ ያመለክታሉ ታሪክን መካድ ደግሞ አያትና ቅድመ አያትን መካድ ማለት ነው። ስለ ሥዕል ክብር የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ታሪክ ምስክር ነው። የታወቀው ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስዘቂሳርያ ስለ ጌታ ሥዕል አጀማመርና አመጣጥ ጽፎ ያቀረበውን ብፁእ አባ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘሸዋበመጽሐፋቸው ጠቅሰውታል። አኛም የጥቅሱን ፍሬ ነገር ቀጥለን ጠቅሰነዋል።

«ንጉሥ ዐብጋር በዑር (ኤዴሣ ከተማ የአገሩ ንጉሥ በመሆን ጌታችን በነበረበት ዘመን ይኖር ነበረ ፤ ስሙም (ልዑካን) ይባል ነበር። ዐብጋር ማለት በከለዳውያን ቋንቋ ቄሣር ማለት ነው። ዐብጋር በዚያ ዘመን በጠና ታሞ ነበር ፤ የጌታችንን ተአምራት በዝና ሰምቶ ይፈውሰው ዘንድ ደብዳቤ ጽፎ ለጌታችን ላከለት ፤ ጌታችንም ደብዳቤውን ከመልእክተኛው እጅ ተቀብሎ ካነበበው በኋላ «ሳያየኝ ያመነኝ ዐብጋር ብፁዕ ነው» ብሎ ዐብጋርን በማመስገን በሱ ስም እንዲፈውሰው ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዱን እንደሚልከለት በመግለጽ መልስ ላከለት። ነገር ግን ከጌታ ጋር ተገናኝቶ የተመለሰው የዐብጋር (ዩካማ) መልእክተኛ ሠዓሊ ስለነበር ከጌታችን ጋር ሲነጋገር ፊቱን በሥዕል ነድፎ (ሥሎ) ከደብዳቤው ጋር ይዞ ተመለሰ። ከዚያም አንደ ደረሰ ከጌታ የተላከውን ደብዳቤ ለታመመው ንጉሥ አነበበለት ፤ ሥዕሉንም አሳየው። በዚያን ጊዜ በሽተኛው ንጉሥ የጌታችንን ቃል ከደብዳቤው ሰምቶና ሥዕሉንም በዓይኑ ተመልክቶ ወዲያው ከሕመሙ እንደ ተፈወሰ ታሪኩ ያስረዳል (አባ ጎርጎርዮስ ፤ የኢ ኦ ተ ቤተ ክርስቲያንታሪክ 1974 1974 119 120)

ይኽው አውሳብዮስ ስለ ጌታችን ሥዕል የሰጠው ምስክርነት እንዲህ የሚል ነው «ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ደሙን እያንጠፈጠፈ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ጎልጎታ በሚጓዝበት ወቅት እያለቀሱ ከሚከተሉት ደጋግ ሴቶች መካከል ቬሮኒካ የተባለች ደግ ሴት የራስዋን መሸፈኛ አውልቃፊቱን አንዲያድፍበት (እንዲጠርግበት ስጌታ ወረወረችለት ፤ ጌታችንም በደምና በላብ የተጠመቀውን ፊቱን ጠርጎ ሥዕለ ሥዕለ ገጹ ማለት የፊቱ መልክ በሻሽዋ ላይ ታትሞ ቀረ »በማለት ከላይ የጠቀስነው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ይመሰክራል።

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ደግሞ ወላዲተ አምላክ በነበረችበት ክፍለ ዘመን የነበረው ሐዋርያው ​​ቅዱስ ያዕቆብ የጌታን ታሪክ (ወንጌል) ሲጽፍ ስለ ወላዲተ አምላክም ብዙ ጽፎአል። በዚህ የያዕቆብ ወንጌል (ያዕቆብ ታሪክ) በተባለው የትውፊት መጽሐፍ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የማርያምን ሥዕል መሃሉ ተጽፎአል።

አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዘቂሳርያና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እንደ መሰከሩት የጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፣ ለወላዲተ አምላክ ፣ ለቅዱሳን መላእክት ፣ ለጻድቃንና ለሰማዕታት ሥዕሎች ከፍ ያለ ክብር እንዲደረግላቸውና የጸጋና የአክብሮት ስግደት እንዲቀርብላቸው ስታስተምር ኖራለች። ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት በሚጸልዩበት ቤተ ክርስቲያንና በቤታቸው በሚገኘው በግል ጸሎት ቤታችው የጌታችንን ፣ የቅድስት ድንግል ማርያምና ​​የቅዱሳንን ሥዕሎች በግድግዳው በመስቀልና የክብር ስግደት በማቅረብሲማፀኑባቸው ኖረዋል።

በዚሁ ሁኔታ የሥዕል ክብር በጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተጠበቀ አስከ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ከቆየ በኋላ ሳይታሰብ በድንገት ከክርስቲያኖቹ መካከል ጥቂቶች ሰዎች የሥዕልን ክብር በመቃወም ተነሡ። በዚሁ ምክንያት በሮምና በቢዛንታይን ግዛቶች ከባድ ክርክርና ሁከት ተቀሰቀሰ። በዚህ ጊዜ በ 797 ዓም የምስራቅቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጉባዔ አድርገው የቅዱሳንን ሥዕሎችማክበርና መሳም (መሳለም) እንደሚገባ ለሥዕሎቹም የአክብሮት ስግደት ማቅረብ ተገቢ መሆኑን በሰፊው አትተው ወስነዋል ... ቀሪውን ከዌብሳይቱ ላይ ያንብብቡ
Oppdatert
8. feb. 2024

Datasikkerhet

Sikkerhet starter med en forståelse av hvordan utviklere samler inn og deler dataene dine. Fremgangsmåtene for personvern og datasikkerhet kan variere basert på bruk, region og alder. Utvikleren har oppgitt denne informasjonen og kan oppdatere den over tid.
Ingen data deles med tredjeparter
Finn ut mer om hvordan utviklere deklarerer deling
Ingen data samles inn
Finn ut mer om hvordan utviklere deklarerer innsamling
Dataene krypteres ved overføring
Du kan be om at data slettes

Vurderinger og anmeldelser

4,5
546 anmeldelser

Nyheter

Sharing Holy Picture is now added
More Holy Pictures Added
Some bugs fixed specially for android 5+ users
bugfix