እርስዎ የሚፈልጉት የግራፍ ካልኩሌተር አፕሊኬሽን ያለማቋረጥና በተሳካ ሁኔታ የሚያገለግል ከፈለጉ፤ በእርግጥም የፍላጎትዎን አግኝተዋል፡፡ቡ
በማትላብ የተዘጋጀው ሳይንሳዊ የግራፍ ካልኩሌተር ከአልጀብራ ጋር የተዋሀደ እና ለሁለተኛ ደረጃ ፣ ለኮሌጅና ፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጣም አስፈላጊ የሆነ የሂሳብ መሳሪያ ሲሆን ለማንኛውም ከመሰረታዊው ካልኩሌትር በርካታ ተጨማሪ ነገሮችን ለሚፈልግ የቀረበ ነው፡፡ በእጅ የሚያዝ ትልቁና ውድ የሆነውን የግራፍ ካልኩሌተር ተክቶና ልክ እንደዝህኛው ካልኩሌተር የሚያገለግል በማንኛውም በአንድሮይድ እና በታብሌት ስልኮች ላይ ተጭኖ እንዲሰራ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
በተጨማሪም በማትላብ የተዘጋጀው የግራፍ ካልኩሌተር በአንድሮይድ መሳሪያ የሰሩትን ሂሳባዊ ስሌት በከፍተኛ ጥራት የሚያሳይ፣ ተጠቃሚው ሂሳባዊ ስሌቱ ቀለል ባለ መንገድ እንዲረዳው የሚያደርግና በግልፅ እንዲያየው ያደርጋል፡፡ ይህ አፕልኬሽን ሁለት ታላላቅ ጠንካራ ጎኖች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ልክ እንደ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር ሲጠቅም ይህም ተማሪዎቹ ከሂሳባዊ ስሌቱ እንዴት የመጨረሻው መልስ እንደተገኘ መመልከትና መማር ያስችላቸዋል፡፡ ሁለተኛው የግራፊክ ችሎታው ፍፁም ያማረ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ካልኩሌተሩን ብቻ ሳይሆን የግራፉን እይታ ያማረ እንዲሆን በማድረግ የኤክስና የዋይ ዋጋ በአውቶማቲክ በማስገኘት በቀላሉ እንዲታይ ያስችላል፡፡
ነፃ (ያለክፍያ) ቅጂ የኢንተርኔት ግኑኝነት ይፈልጋል እንደገና ማስታወቂያዎችንም የያዘ ነው፡፡ ወደ ዋናው ቅጂ (PRO) ያሻሽሉት
ቪድዮ: https://youtu.be/6BR8Lv1U9kA
ሳይቱን በመመሪያና በምሳሌ ጋር ለመርዳት https://help.mathlab.app
ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር
* ሒሳባዊ (አሪትሜቲክ) ምልክቶች +,-,*,/,÷
* እስኴር ሩት፣ ክዩብ ሩት እና ትላልቅ ሩቶች (የ√ ቁልፍ መጫን)
* ኤክስፖነንት ሎጋሪዝም (ln, log)
* ትሪጎኖሜትሪክ ፈንክሽንስ sin π/2, cos 30°,...
* ሀይፐርቦሊክ ፈንክሽንስ ሳይን sinh, cosh, tanh, ... (የ "e" ቁልፍ መጫን ለማብራት/ለማጥፋት)
* ኢንቨርስ ፈንክሽንስ (ቀጥታ ፈንክሽን ቁልፎችን መጫን)
* ውስብስብ ቁጥሮች ፣ ሁሉም ፈንክሽኖች ውስብስብ ሀሳቦችን ይደግፋሉ
* ዴሪቬቲቭስ sin x' = cos x, ... (x^n ቁልፍ መጫን)
* ሳይንሳዊ ማስታወሻ (ሜኑ ላይ እንዲሰራ ተደርጓል)
* መቶኛ (ፐርሰንት) ሞድ
* ሴቭ/ሎድ ታሪክ
የግራፍ ካልኩሌተር
* ለግራፍ በርካታ ስራዎች አሉት
* ያልተገለፁ ስራዎች እሰከ ሁለተኛ ዲግሪ (ኢሊፕስ 2x^2+3y^2=1, ወዘተ)
* ፖላር ግራፎች (r=cos2θ)
* ፓራሜትሪክ ፈንክሽኖች፣ እያንዳንዱ በአዲስ መስመር ማስገባት (x=cos t, y=sin t)
* ፈንክሽን ሩትና ክሪቲካል ነጥቦች በግራፍ ላይ፣ ከፈንክሽን ላይ በስተግራ በኩል ያለው የማረጋገጫ ሣጥን (ቼክቦክስ) መምረጥ በግራፍ ላይ ኮኦርዲኔቶችን ያሳያል፡፡ በግራፉ በላይኛው ሜኑ ላይ የግራፉን ቁልፍ ክሊክ በማድረግ የኮኦርዲኔቶችን ዝርዝር ያሳያል፡፡
* ግራፍ ኢንተርሴክሽንስ (x^2=x+1)
* የፈንክሽን ዋጋ እና እስሎፕ ለማግኘት
* የመሸበለልና ስፋቱ የሚስተካከል ግራፍ ለመስራት
* ለማስፋትና ለማጥበብ
* ሙሉ ስክሪን ግራፍ በላንድስኬፕ አገላለፅ እንዲታይ
* የፈንክሽን ሰንጠረዦች
* ግራፎችን እንደ ምስል ለመቀየርና ለማቆየት
* ሰንጠረዦችን እንደ “csv” ለማቆየት
የክፍልፋይ ካልኩሌተር
* ቀላልና ውስብስብ ክፍልፋዮችን 1/2 + 1/3 = 5/6
* ቅልቅል ቁጥሮች ፣ ዋጋ ለማስገባት ስፔስን መጠቀም 3 1/2
አልጄብራ ካልኩሌተር
* ሊኒየር ኢኴሽኖች x+1=2 -> x=1
* ኳድራቲክ ኢኴሽኖች x^2-1=0 -> x=-1,1
* ለከፍተኛ ፖሊኖሚያሎች ግምታዊ ሩት ለመስጠት
* የሊኒየር ኢኴሽኖች ዘዴ ፣ በአንድ መስመር አንድ ኢኴሽን መፃፍ፣ x1+x2=1, x1-x2=2
* ለፖሊኖሚያል ለረጅም ተካፋዮች
* ለፖሊኖሚያል ማስፋፊያ ፣ ለፋክተሪንግ
ማትሪክስ ካልኩሌተር
* ለማትሪክስና ለቬክተር ስራ
* ለዶት ውጤቶች (መጫን*) ክሮስ ፕሮዳክት
* ዲተርሚናንት፣ ኢንቨርስ፣ ኖርም፣ ትራንስፖዝ፣ ትሬስ
ላይብራሪ
* ተጠቃሚው የሚገልፃቸው ኮንስታንቶችና ፈንክሽኖች (PRO)
* ሴቭ/ሎድ አገላለፆች