ሁቱትሲ

يتضمن إعلانات
+100
عملية تنزيل
تقييم المحتوى
الجميع
صورة لقطة الشاشة
صورة لقطة الشاشة
صورة لقطة الشاشة
صورة لقطة الشاشة

لمحة عن هذا التطبيق

ሁቱትሲ "Left To Tell" በኣማርኛ የተተረጎመ የወጣቷ ልብ አንጠልጣይ ትውስታዎች የያዘ መፅሐፍ ነው።

ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ከስቲቭ ኤርዊን ጋር በመተባበር የጻፈችው ሁቱትሲ የተሰኘው መጽሐፍ ምናልባት ስለ ሩዋንዳ ከተጻፉት መጻሕፍትም ሆነ ከታዩት ፊልሞች በላይ የፍጅቱን አሰቃቂነትና ዘግናኝነት ገላጭ ነው ማለት ይቻላል።
.
ምክንያቱምምክንያቱም ከሰሚ ሰሚ የወረደ ታሪክ ሳይሆን እጅግ ከስድስት ቤተሰብ አባላት ከግድያው የተረፈችው አንዲት ቱትሲ ወጣት ከአንድ በማይበልጥ መጸዳጃ ቤት ቱትሲ ጓደኞቿ ጋር ከአሁን አሁን ተገደልኩ እየተጨነቀች የሃይማኖት ጽናቷ እንዴት ለሦስት ወር እንዳኖራትና በኋላም እንዴት ነጻ ወጥታ ወልዳ ለመሳም የበቃች መሆኗን የሚተርክ ታሪክ ፡ የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተዋንያንን ፍርድ ቤት እንዳቀርብ በተባበሩት መንግስታት በከፍተኛ የሕግ አማካሪነት ተቀጥሬ በሠራሁበት ጊዜ ከሰማኋቸው በላይ ልብን ሰቅዞ የሚይዝና አእምሮን የሚያናውጥ ታሪክ ይኖራል ብዬ አልገመትኩም ነበር።
.
ሆኖም በዚህ መጽሐፍ አጋጥሞኛል። ስሜታዊነት አይነካኝም ፣ መንፈሴ በሚያየውና በሚሰማው የማይረበሽ ጠንካራ ሰው ነኝ ባይ ይህንን መጽሐፍ በሚያነብበት ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ዓይኖቹ በእንባ ችፍ ችፍ ማለታቸው አይቀርም።
.
የኢማኪዩሌ ታሪክ ምንጩ ወይንም የስቃይዋ ምክንያት የተወሳሰበ አይደለም። መንስኤው ርህራሄ የሚወልደውን የሰብአዊ ስሜትን ደምስሶ ከጥላቻ በላይ ጥላቻ ወልዶ ሰውን ከአውሬነት በታች የሚያውለው የዘር ጥላቻ ነው።
.
የዘር ጠላቻ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ለሌላው ሰብዓዊ ፍጡር ሊኖረው የሚገባውን ሐዘኔታና ርህራሄ ከሰው ልብ ፈልቅቆ አውጥቶ ከአውሬ በባሰ ጭካኔ ይተካዋል። በሩዋንዳው የዘር ፍጅት የተፈጸመውን አራዊት ከሚያደርጉት ጋር ማወዳደር የአራዊትን ስም ማጥፋት ይሆናል። የትኛው አውሬ ነው ሕጻናትን ከታትፎ እንደ ጌሾ በሙቀጫ የሚወቅጠው؟ የትኛው አውሬ ነው በኢማኪዩሌ ወንድም ላይእንደተፈጸመው ቆራርጦ ክምር ላይ የሚጥል؟ የትኛው አውሬ ነው የሰውን ጭንቅላት በገጀራ ሰውዬውን በዝግታ እንዲሞት የሚያደርገው؟ የትኛው አውሬ ነው የአምስት ልጆችን እናት ፊት ደፍሮ ፊቷ አምስቱንም ልጆቿንና ባሏን አንድ በአንድ የሚከትፈው؟ ከአክራሪ ሁቱዎች በስተቀር የትኛውም አውሬ አያደርገውም።
.
የሩዋንዳ የዘር ፍጅት የሰው ልጅ ጭካኔ ልክ የታየበት ነው። ተመሳሳይፍጅትና ጭካኔ የተፈጸመባቸው የናዚዎችና የአርመኖች እልቂቶች እንደሩዋንዳው መንስኤአቸው የዘር ጥላቻ ነበር። ኢማኪዩሌ በመጽሐፏ የጠቀሰችው የዘር ፍጅቱ ቀስቃሽና ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ቲዩኔስት ባጎስራ ፍርድ ቤት አቅርቤው ዳኞቹ ክሱን አንብበውለት ጥፋተኛ ነህ አይደለህም ብለው ፈገግ ‹ناقلات ጥፋተኛ ጦር ይዋጋ ነበር።
.
መጽሐፉ ከእንግሊዝኛ የተተረጎመ ሲሆን ፤ ምናልባትም የአማርኛው ትርጉም ድርጊቶቹን ከእንግሊዝኛው በተሻለ ይገልጻቸዋል ማለት ይቻላል። ተርጓሚው የሥነ- ጽሑፍ ምሁር እንደመሆናቸው መጠን አገላለጹ ከኢማኪዩሌ በልጦ ቢገኝ አይገርምም። የቃላቱ ገላጭነት ፣ የአረፍተ ነገሮቹ አሰካክ ፣ የቋንቋው አወራረድና በጠቅላላው የአማርኛው ውበት ከታሪኩ መሳጭነት ጋር ሆኖ መጽሐፉን ማንበብ ከተጀመረ መልሶ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው።
.
ይህ መጽሐፍ የብሔር ጥላቻ የሚፈጥሩ ፖሊሲዎችን ለሚቀርጹና በብሔረሰብ ስም ህዝብን ከፋፍለው ጥላቻ ለሚያስፋፉ ሰዎችም ሆኑ መዋቅርት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንብቦ እንዲማርበት እማፀናለው
تاريخ التحديث
02‏/07‏/2023

أمان البيانات

يبدأ الحفاظ على أمان بياناتك بفهم الطريقة التي يتّبعها مطوِّرو التطبيقات لجمع بياناتك ومشاركتها. قد تختلف خصوصية البيانات وممارسات الأمان حسب كيفية استخدامك للتطبيق ومنطقتك وعمرك. يوفّر مطوِّر التطبيقات هذه المعلومات وقد يعدِّلها بمرور الوقت.
قد يشارك هذا التطبيق أنواع البيانات هذه مع جهات خارجية.
الموقع الجغرافي والنشاط على التطبيق و2 نوع آخر من البيانات
قد يجمع هذا التطبيق أنواع البيانات هذه.
الموقع الجغرافي والنشاط على التطبيق و2 نوع آخر من البيانات
يتم تشفير البيانات أثناء النقل
يتعذّر حذف البيانات

الجديد

Initial Release