Gibre Himamat ግብረ ሕማማት

100+
Nedlastinger
Egnethet
Alle
Skjermbilde
Skjermbilde
Skjermbilde
Skjermbilde
Skjermbilde
Skjermbilde
Skjermbilde
Skjermbilde

Om denne appen

Gibre Himamat er en etiopisk ortodoks Tewahedo-bok som leses i Holy Week, den siste uken av fasten. Boken inneholder opplesninger av palmesøndag, hellig mandag, hellig tirsdag, hellig onsdag (spion onsdag), tung torsdag (hellig torsdag), langfredag ​​(hellig fredag), hellig lørdag og påske. Boken inneholder opplesninger fra Holy Bible, Ortodokse kanoniske bøker, Synaxarium, Jesus Kristus mirakler, Miracle of Saint Mary, Prophecies, Prayer Books, Haymanote Abew, Prayer of Covenant, Gedles og flere etiopiske ortodokse Tewahedo kirkebøker.

Det hemmelige formålet med denne boken er å minne oss på at Herren har gitt oss smerte, død, evig frihet og ære i sin oppstandelse, og at han er livets Gud uten smerter og død, lest og øvd hver dag i denne hellige uken


Følgelig er det generelle mønsteret for bønnen og gudstjenesten til Gibre Himamat inneholdt i denne boken, og det er vårt oppriktige håp at prestene og menighetene kan holde boka og følge den.

መጽሐፈ ግብረ ሕማማት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታችንነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀል የሚዘከርበትና በሰሙነ ሕማማት የሚነበብ ታላቅ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ፣ ከሥርዓት መጻሕፍት ፣ ከትንቢት ፣ ከድርሳናት ፣ ከተአምራት ፣ ከመዝሙራት ፣ ከተግሣጻት ፣ ከሃይማኖተ አበው ፣ ከኪዳን መጽሐፍ ፣ ከመጽሐፈ ስንክሳርና ከአበው መጻሕፍት የተውጣጡ ትምህርቶችንና የጸሎት ክፍሎችን ከሆሣዕና ዋዜማ እስከ ትንሣኤ ባሉት ስምንት ቀናንት በሰዓታት ተከፋፍሎ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።

የመሠረቱና ታሪካዊ አመጣጡም ከአባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ተያይዞ የመጣ ነው። ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለሐዋርያት እየተገለጸ እስከ አርባ ቀን ድረስ መጽሐፈ ኪዳንንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምራቸው ቈይቶ። በአርባ ቀኑም ሐዋርያትን በአንብሮተ እድ ሹሟቸውና ባርኳቸው አርጓል። (ማር ፲፮ ፲ህ። ሉቃ ፳፬ ፤ ፶፩። የሐዋ ሥራ ፩-፱)

ከዚህም በኋላ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ካሉ ምዕመናን ጋር ጾም መጾምንና ትንሣኤውን ማክበር ጀመሩ። በዚህ ጊዜ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው በደነገጉት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፥ ስለ ሰሙነ ሕማማት «ወአንትሙሰ ተዐቅቡ ወግበሩ ተዝካረ ሕማማቲሁእናንተ ግን ጠብቃችሁ የመከራ መስቀሉ መታሰቢያ የሆነውን ሕማማቱን አድርጉ አክብሩ» ሲሉ አዝዘዋል። (ትእዛዝ ፴፩)

ሆኖም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ይፋጠኑ ነበረና እንደ ዛሬው ሁሉ ጊዜውን አልወሰኑትም ነበር። ከሐዋርያት ቀጥለው የተነሱ ሊቃውንትም ቢሆኑ እንደዚሁ በዐተ ጾምን ከጥር ፲፩ ቀን እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ከጾመ። በኋላ ሰሙነ ሕማማትን ደግሞ ከዐቢይ ጾም ለይተው ከመጋቢት ፳፪ እስከ መጋቢት ፳፰ ቀን በመጾም መጋቢት ፳፱ ቀን ትንሣኤውን ያከብሩ ነበር። ይህ ሥርዓት ሲያያዝ እስከ ድሜጥሮስ ዘመን ደረሰ።


ከ፩፻፹፰ እስከ ፪፻፴ ዓ.ም የነበረው ሊቀ ጳጳስ ድሜጥሮስ በአዘጋጀው የጊዜ መቁጠሪያ (ባሕረ ሐሣብ) ሰሙነ ሕማማት ከዐቢይ ጾም ቀጥታ እንዲሆን ተወስኖአል። ቤተ ክርስቲያንም በቀመረ ድሜጥሮስ ዓመታትን በንዑስ ፤ በማዕከላዊና በዐቢይ ቀመር እየቀመረች አጽዋማት የሚገቡበትንና በዓላት የሚውሉበትን ጊዜ ለምዕመናን ታሳውቃለች።

ስለሆነም የሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎትና አገልግሎት ሁኔታ ከቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮት ጋር የተያያዘ ቢሆንም አሁን ያለውን ሥርዓት የያዘ ግብረ ሕማማት ፤ የተሰኘው መጽሐፍ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ የዋለው ከጌታ ልደት በኋላ በ፲፬ኛው ምዕት ዓመት ነው።

ከ፩ሺ፫፻፵ እስከ ፩ሺ፫፻፹ ዓ.ም የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ብርሃነ ዐዜብ ከዐረብኛ ወደ ግእዝ እንደተረጎሙት ቀደም ሲል በግእዝ ብቻ ታትሞ በነበረው የግብረ ሕማማት መጽሐፍ ውስጥ ተገልጦአል።

የመጽሐፉ ስያሜም ከጥንተ ስሙ ጀምሮ ግብረ ሕማማት እንደሚባል በመጽሓፉ ውስጥ በብዙ ክፍል ተጠቅሶ ይገኛል። ለዚሁም በቂ የሆነ ምሥጢራዊ ምክንያት እንዳለው ይታመናል።

ምሥጢራዊ ዓላማውም ጌታ በሕማሙ ሕማማችንን ፤ በሞቱ ሞታችንን ፤ በትንሣኤው ዘለዓማዊ ነፃነትንና ክብርን ያጐናጸፈን መሆኑን ከማስገንዘቡም በላይ በባሕርዩ መከራና ሞት የሌለበት ሕያወ ባሕርይ አምላክ መሆኑ በሰሙነ ሕማማት በየአንዳንዱ ቀን ይነበባል ይተረካልም።


በዚህ መሠረት የሰሙነ ሕማማት ጸሎትና አገልግሎት ጠቅላላ ሥርዓት በዚህ መጽሓፈ ግብረ ሕማማት በየክፍሉ ተጽፎ ስለሚገኝ ካህናትም ምዕመናንም መጽሐፉን በመያዝ ሥርዓቱን ለመከታተል ያመቻል የሚል ጽኑእ ተስፋ አለን።
Oppdatert
22. jan. 2024

Datasikkerhet

Sikkerhet starter med en forståelse av hvordan utviklere samler inn og deler dataene dine. Fremgangsmåtene for personvern og datasikkerhet kan variere basert på bruk, region og alder. Utvikleren har oppgitt denne informasjonen og kan oppdatere den over tid.
Ingen data deles med tredjeparter
Finn ut mer om hvordan utviklere deklarerer deling
Ingen data samles inn
Finn ut mer om hvordan utviklere deklarerer innsamling
Dataene krypteres ved overføring
Dataene kan ikke slettes