ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ.

1978 • 101 ደቂቃዎች
PG
ደረጃ
ይህ ንጥል አይገኝም

ስለዚህ ፊልም

ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ. በ1970 ዓም የተፈጠረ አንድ የአሜሪካ ኮሜዲ ፊልም ነው።
የፊልሙ ታሪክ የተመሠረተው በ1960 ዓም በተመሳሳይ ስም በወጣው ዘፈን ከጂኒ ራይሊ፣ «ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ. » ነበረ። ይሄ በአሜሪካ አገር በነዚህ ዓመታት መካከል የተከሠቱት የባህል ለውጦች በደንብ ይዘግባል።
በታሪኩ ውስጥ፣ ስቴላ ጆንሰን በሃርፐር ቫሊ ኦሃዮ የምትገኝ ባልዋም ያረፈባት መልከ መልካም ብቸኛ እናት ነች። ለኮስሞቲክ ድርጅት የሰውን በር በማንኳኳት ኮስሞቲክ ትሸጣለች፣ ከዚህም ጭምር በሕይወት ለመደሠት አትፈራም። ሴት ልጅዋ ዲ 14 ዓመት ስትሆን የሃርፐር ቫሊ ፪ኛ ደረጃ ተማሪ ነች።
አንድ ቀን ዲ ከትምህርት ቤት ተመልሳ የሃርፐር ቫሊ ወላጆች-አስተማሮች ማኅበር ደብዳቤ ለናትዋ ለስቴላ አመጣች። በደብዳቤውም ዘንድ፣ የስቴላ አለባበስ የመንደሩን ግብረ ገብ ስለማትከብር፣ ለማኅበሩ ደስታ መንገድዋን ካልቀየረች በቅጣት ልጅዋ ከትምህርት ቤቱ ትወገዝ ነበር። የማኅበሩም አለቃ በጣም ጉረኛ ትዕቢተኛ የሆነችው ፍሎራ ሲምሰን-ራይሊ ትባላለች።
በማኅበሩ ግብዝነት ተናድዳ፣ ስቴላ እራስዋ በሚከተለው ማኅበር ስብሰባ ድንገት ገባች። የማኅበር አባላት ምስጢሮችን ገልጣ ግብዞች እንደ ሆኑ በገሃድ አወጣች።
ከዚህ በኋላ አንድ ሌላ ደብዳቤ ከድንጋይ ጋር በስቴላ መኖርያ ቤት በመስኮት ብርጭቆ በኩል ይደርሳል። ከመንደሩ እንድትወጣ ይላል። ከዚህም በኋላ በተረፈው ፊልም ስቴላ በብልሃቶችዋ ቂምዋን አበቀለች፣ የመንደሩንም ኗሪዎች አሳብ ቀየረችና እንኳን እራስዋ የማኅበር አለቃ፣ በመጨረሻም የመንደሩም ከንቲባ ዕጩ ሆነች። አዲስ ባል ደግሞ አግኝታለች።
እንደገና በ1973 ዓም ባርባረ ኢደን ጋር ሃርፐር ቫሊ ፒ. ቲ. ኤ. ተሠራ።
የተሰጠ ደረጃ
PG