ስለዚህ ትርዒት

Gunsmoke ከ1955 እስከ 1975 እ.ኤ.አ. የተሠራ አሜሪካዊ ድራማ ትርዒት ነበረ። በአሜሪካ አገር ምዕራብ፣ በዶጅ ሲቲ፣ ካንዛስ 1877 እ.ኤ.አ. አካባቢ፣ ብዙ ወንጀለኞች በሚደርሱበት ከተማ ሲሆን የቦታው ዋና ባለሥልጣን ፣ ማርሻል ማት ዲሎን ሕጉን ለመመሥረት ሀላፊነት ያለው ነው። ለሀያ አመት በመቆየቱ በአሜሪካ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ እጅግ የተወደደ ፕሮግራም ሆኖ ይታወሳል።
233 የ30 ደቂቃ ክፍሎች ከተሠሩ በኋላ፣ 402 የአንድ ሰዓት ክፍሎች ተጨመሩ።