እኛና አብዮቱ

· TSEHAI Publishers
4.0
1 review
Ebook
454
Pages
Eligible

About this ebook

በጡረታ እስከተገለልኩበት ጊዜ ድረስ አብዮቱን በግምባር ቀደምትነት ከመሩት የደርግ አባላት ውስጥ አንዱ ነኝ። ደርግ ከመመሥረቱ በፊት በአገራችን የተካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ምን ይመስሉ እንደነበር፣ ደርግ በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ፣ ፖለቲካዊ ሥልጣንም እንዴትና ለምን ሊይዝ እንደበቃ፣ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ ደግሞ መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ በማምጣት አገራችን ከኋላ ቀርነትና ከድህነት ተላቅቃ የሠለጠነችና የበለጸገች እንድትሆን ያደረገውን ጥረትና የከፈለውን መስዋዕት በቅርብና በዝርዝር አውቃለሁ።

ደርግ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ፖሊሲዎችን ሲነድፍ፣ የተለያዩ ሕጎችን ሲደነግግ፣ ልዩ ልዩ ውሣኔዎችን ሲያስተላልፍ፣ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን ሲያወጣ፣ በብዙዎቹ ስብሰባዎች በመገኘት የድጋፍ ድምጽ ሰጥቻለሁ፤ አፈጻጸማቸውንም ተከታትያለሁ።

በነበረኝ ሥልጣን ምክንያት ከሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለነበረኝ በየትኛውም አካባቢና መሥሪያ ቤት የተከናወኑ ሥራዎችንና የተፈፀሙ ስህተቶችን ከሞላ ጎደል አውቃለሁ። በዚህ የተነሣ የደርግን ታሪክ የመፃፍ ሃላፊነት እንዳለብኝ ይሰማኛል።

እስረኛ በነበርኩበት ጊዜ በመጽሐፍ መልክ አዘጋጅቼ ለሕዝብ ለማቅረብ ባልችልም ከእስር ከተፈታሁ በኋላ ግን የደርግን ታሪክ ለመጻፍ ተነሳሳሁ። በተበታተነ ሁኔታ የመዘገብኳቸውን ታሪካዊ ክንውኖች በማሰባሰብና በኢትዮጵያ የአብዮት ሂደት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበራቸውን ወዳጆቼንና የሥራ ባልደረቦቼንም በማነጋገር የደርግንና የአብዮቱን ታሪክ ለመመዝገብ ጥረት አደረኩ።

ባልጠበቅኩት ሁኔታ ከእሥር ቤት ከወጣሁ በኋላ አሁን ያለውና በተከታታይ የሚመጡት ትውልዶች የታሪካቸው አካል ስለሆነው የደርግ ታሪክ በከፊልም ቢሆን እንዲያውቁ የተወሰኑ ጉዳዮችን ብቻ የሚተርክ ይህን መጽሐፍ አዘጋጅቻለሁ።

መጽሐፉ በጥድፊያ ሳይሆን በጥንቃቄና በጥልቀት መነበብ አለበት የሚል እምነት አለኝና መልካም ንባብ እንዲሆንልዎ እመኛለሁ።

Ratings and reviews

4.0
1 review
A Google user
September 27, 2017
It's our History whatever happened in past.
Did you find this helpful?

Rate this ebook

Tell us what you think.

Reading information

Smartphones and tablets
Install the Google Play Books app for Android and iPad/iPhone. It syncs automatically with your account and allows you to read online or offline wherever you are.
Laptops and computers
You can listen to audiobooks purchased on Google Play using your computer's web browser.
eReaders and other devices
To read on e-ink devices like Kobo eReaders, you'll need to download a file and transfer it to your device. Follow the detailed Help Center instructions to transfer the files to supported eReaders.