ይህ መተግበሪያ የሸሪዓ ዕውቀትን ከትክክለኛ ምንጮች፣ በስርዓት እና በደረጃ ለመማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በመተግበሪያው ምን ያገኛሉ?
ሰፊ የትምህርት አይነቶችን ያካተተ ሲሆን፦
➳ የዓቂዳ፣ የመንሃጅ፣ የአዳብ፣ የፊቅህ፣ የሐዲስ ትምህርቶች በአንድ ላይ ተካተዋል።
የተደራጀ የትምህርት ደረጃዎች
ትምህርቶቻችን በሶስት ዋና ዋና ደረጃዎች የተከፋፈሉ ሲሆን፣ ተማሪዎች በአቅማቸው መሰረት እንዲጓዙ ያግዛል፦
የመጀመሪያ ደረጃ (المستوى الأول):
መሰረታዊ የሆኑ የዓቂዳ እና የፊቅህ ኪታቦች (እንደ ኹዝ ዓቂደተክ፣ ሠላሰቱል ኡሱል፣ አል-አርበዑን ነወዊያ፣ ወዘተ)።
ሁለተኛ ደረጃ (المستوى الثاني):
ኪታቡ ተውሒድ፣ ከሽፉ ሹቡሃት፣ የኢማም ሻፊኢ ኢስባቱ ሷፋት፣ ወዘተ።
ሦስተኛ ደረጃ (المستوى الثالث)፡
ለወደፊት የሚካተቱ ተጨማሪ ኪታቦች(እንደ ሑልየቱ ጧሊቢል ዒልም፣ ዐቂደቱል ዋሲጢያ፣ ዑምደቱል አሕካም፣ የአጅሩሚያ ኢዕራብ፣ ወዘተ)።
አፑን ለአጠቃቀም ልዩ እና ምቹ የሚያደርጉት ባህሪያት፦
• ደርሶችን ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ በቅደም-ተከተል የሚያስተምር።
• ትምህርቱን ሲጨርሱ ራሶን የሚፈሹበት ፈተናዎች ያሉት።
• በትምህርቱ መሃል አስፈላጊ ነጥቦችን በቀላሉ መፃፍ የሚያስችል ጥሩ ማስታወሻ መያዣ ያለው።
• የደርሶች ማውጫ በየዘርፉ በጥራት የተከፋፈለበት።
• የፈለጉትን ደርስ በቀላሉ መልሰው ለማግኘት ምልክት ማድረግ የሚያስችል።
• ከቅጅዎቹ መካከል የመረጡትን ለሌሎች ማጋራት (Share) የሚያስችል አማራጭ።
• አፑን ለአጠቃቀም አመቺ የሚያደርጉት ማስተካከያዎች ያሉት።
• ደርሱን አቋርጠው በሌላ ጊዜ ማዳመጥ ቢፈልጉ በትክክል ካቆሙበት ሰከንድ የሚጀምር።
اللهم علمنا ما ينفعنا وانفعنا بما علمتنا إنك أنت الجواد الكريم
(አላህ ሆይ! የሚጠቅመንን እውቀት አስተምረን፣ ባስተማርከን እውቀትም ተጠቃሚ አድርገን፤ አንተ እጅግ ለጋስ እና ቸር ነህ።)
ኢስላማዊ ትምህርቶችን በቀላሉ፣ በተደራጀ መልኩ እና በማንኛውም ቦታ ሆነው ለመማር የሚያስችልዎት