የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭ እና ማሳወቂያ

3.8
149 ሺ ግምገማዎች
1 ቢ+
ውርዶች
የይዘት ደረጃ አሰጣጥ
ሁሉም ሰው
የቅጽበታዊ ገፅ ዕይታ ምስል
የቅጽበታዊ ገፅ ዕይታ ምስል
የቅጽበታዊ ገፅ ዕይታ ምስል
የቅጽበታዊ ገፅ ዕይታ ምስል
የቅጽበታዊ ገፅ ዕይታ ምስል
የቅጽበታዊ ገፅ ዕይታ ምስል
የቅጽበታዊ ገፅ ዕይታ ምስል

ስለዚህ መተግበሪያ

የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭ እና የድምፅ ማሳወቂያዎች የእርስዎን Android ስልክ ወይም ጡባዊ በመጠቀም መስማት በተሳናቸው እና የመስማት ችግር ባለባቸው ሰዎች መካከል የዕለት ተዕለት ውይይቶችን እና የዙሪያ ድምጾችን ይበልጥ ተደራሽ ያደርጓቸዋል።

በአብዛኛዎቹ መሣሪያዎች ላይ የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭ እና የድምፅ ማሳወቂያዎችን በእነዚህ ደረጃዎች በቀጥታ መድረስ ይችላሉ፡-
1. የመሣሪያዎን የቅንብሮች መተግበሪያ ይክፈቱ።
2. ተደራሽነትን መታ ያድርጉ፣ ከዚያም ለመጀመር በሚፈልጉበት መተግበሪያ ላይ በመመስረት የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭን ወይም የድምፅ ማሳወቂያዎችን መታ ያድርጉ።
3. የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭን ወይም የድምፅ ማሳወቂያዎችን ለመጀመር የተደራሽነት አዝራሩን፣ ምልክትን ወይም ፈጣን ቅንብርን (https://support.google.com/accessibility/android/answer/7650693) ይጠቀሙ።

የድምፅ ማሳወቂያዎች፦
• በቤት ውስጥ በሚፈጠሩ ድምፆች (ለምሳሌ የጭስ ማንቂያ፣ ሳይረን፣ የህፃን ድምፆች) ላይ በመመስረት አደገኛ ሊሆኑ ስለሚችሉ ሁኔታዎች እና የግል ሁኔታዎች ማሳወቂያ ያግኙ።
• የቤት መገልገያዎችዎ ድምፅ ሲያሰሙ ማሳወቂያዎችን ለማግኘት ብጁ ድምጾችን ያክሉ።• በእርስዎ ተንቀሳቃሽ መሣሪያ ወይም ተለባሽ ብልጭ ድርግም በሚል ብርሃን ወይም ንዝረት አማካኝነት ማሳወቂያዎችን ያግኙ።
• የጊዜ መስመር ዕይታ በዙሪያዎ ምን እየተከናወነ እንደነበረ እንዲያዩ በታሪክ ወደኋላ (በአሁኑ ጊዜ በ12 ሰዓታት የተገደበ ነው) እንዲመለሱ ያስችልዎታል።

ቅጽበታዊ ወደ ጽሁፍ ግልባጭ፦
• በቅጽበት ወደ ጽሁፍ ይገለብጣል። ልክ ቃላት ሲነገሩ ጽሁፍ በመሣሪያዎ ላይ ይታያል።
• ከ80 በላይ ከሆኑ ቋንቋዎች እና ዘዬዎች መካከል ይምረጡ እና በፍጥነት በሁለት ቋንቋዎች መካከል ይቀያይሩ።
• እንደ ስሞች ወይም የቤት ውስጥ ዕቃዎች ያሉ እርስዎ በተደጋጋሚ የሚጠቀሙባቸውን ብጁ ቃላት ያክሉ።
• የሆነ ሰው የእርስዎን ስም ሲጠራ መሣሪያዎ እንዲነዝር አድርገው ያቀናብሩት።
• በእርስዎ ውይይት ውስጥ ምላሾችን ይተይቡ። የመሣሪያዎን ቁልፍ ሰሌዳ ያምጡ እና ቀጣይነት ላለው ውይይት ቃላትዎን ይተይቡ። የጽሁፍ ግልባጮች እርስዎ በሚተይቡበት ጊዜ አሁንም ይታያሉ።
• በእርስዎ አካባቢ ላይ ካለ ጩኸት ጋር በማነጻጸር የተናጋሪውን የድምፅ መጠን ይመልከቱ። እርስዎ በሚናገሩበት ጊዜ የድምፅ መጠንዎን ለማስተካከል ይህን የድምፅ አመልካች መጠቀም ይችላሉ።
• ለተሻለ የኦዲዮ መቀበያ በባለገመድ ማዳመጫዎች፣ በብሉቱዝ ማዳመጫዎች እና በዩኤስቢ ማይክ ውስጥ የሚገኙ ውጫዊ ማይክሮፎኖችን ይጠቀሙ።

የጽሁፍ ግልባጭን መልሰው መመልከት፦
• የጽሁፍ ግልባጮችን ለ3 ቀናት ለማስቀመጥ ይምረጡ። የተቀመጡ የጽሁፍ ግልባጮችን ወደ ሌላ ቦታ መቅዳት እና መለጠፍ እንዲችሉ ለ3 ቀናት በመሣሪያዎ ላይ ይቆያሉ። (በነባሪ፣ የጽሁፍ ግልባጮች አይቀመጡም።)
• በተቀመጡ የጽሁፍ ግልባጮች ውስጥ ይፈልጉ።
• የጽሁፍ ግልባጭ ውስጥ ያለውን ጽሁፍ ለመቅዳት እና ለመለጠፍ ይንኩ እና ይያዙ።

መስፈርቶች፦
• Android 6.0 (ማርሽሜሎው) እና ከዚያ በላይ።

የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭ እና የድምፅ ማሳወቂያዎች በአሜሪካ ውስጥ ቀዳሚ የመስማት የተሳናቸው እና የመስማት ችግር ያላቸው ዩኒቨርሲቲ ከሆነው ጋላውዴት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተሠራ ነው።

ግብረመልስ ለመስጠት እና የምርት ዝማኔዎችን ለመቀበል https://groups.google.com/forum/#!forum/accessibleን ይቀላቀሉ። የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭ እና የድምፅ ማሳወቂያዎችን መጠቀም ላይ እገዛ ለማግኘት https://g.co/disabilitysupport ላይ ያግኙን።

የፈቃዶች ማስታወሻ
ማይክሮፎን፦ የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭ በዙሪያዎ ያለውን ንግግር ወደ ጽሁፍ ለመገልበጥ የማይክሮፎን መዳረሻ ያስፈልገዋል። የጽሁፍ ግልባጩ ከተሰናዳ በኋላ ኦዲዮው አይከማችም። የድምፅ ማሳወቂያዎች በእርስዎ ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ ድምጾችን ለማዳመጥ የማይክሮፎን መዳረሻ ያስፈልጋቸዋል። እንዲሁም ማሰናዳት ከተጠናቀቀ በኋላ ኦዲዮው አይከማችም።
የተደራሽነት አገልግሎት፦ ይህ መተግበሪያ የተደራሽነት አገልግሎት ስለሆነ የእርስዎን እርምጃዎች መመልከት ይችላል።
የተዘመነው በ
6 ፌብ 2024

የውሂብ ደህንነት

ደህንነት ገንቢዎች ውሂብዎን እንዴት እንደሚሰበስቡ እና እንደሚያጋሩ ከመረዳት ይጀምራል። የውሂብ ግላዊነት እና ደህንነት ልማዶች በአጠቃቀምዎ፣ ክልልዎ እና እድሜዎ መሰረት ሊለያዩ ይችላሉ። ገንቢው ይህንን መረጃ አቅርቧል እናም በሌላ ጊዜ ሊያዘምነው ይችላል።
ምንም ውሂብ ለሶስተኛ ወገኖች አልተጋራም
ገንቢዎች ማጋራትን እንዴት እንደሚገልፁ ተጨማሪ ይወቁ
ይህ መተግበሪያ እነዚህን የውሂብ አይነቶች ሊሰበስብ ይችላል
የግል መረጃ፣ ኦዲዮ እና 3 ሌሎች
ውሂብ በመጓጓዣ ውስጥ ተመስጥሯል
ውሂብ ሊሰረዝ አይችልም
ገለልተኛ የደህንነት ግምገማ

ደረጃዎች እና ግምገማዎች

3.8
146 ሺ ግምገማዎች
Amino Abagerp
13 ኖቬምበር 2023
ምንም አይልም
3 ሰዎች ይህን ግምገማ አጋዥ ሆኖ አግኝተውታል
ይህን አጋዥ ሆኖ አግኝተውታል?

ምን አዲስ ነገር አለ

• የቀጥታ ጽሁፍ ግልባጭ፦ ግንኙነት ባይኖርም ይበልጥ እንከን የለሽ እንዲሆን ወደ ጽሁፍ መገልበጥን ያንቁ።