የGoogle አውቶሞቲቭ ቁልፍ ሰሌዳ ስለ Google ቁልፍ ሰሌዳ እርስዎ የሚወዱት ነገር ሁሉ አለው፦ ፍጥነት፣ አስተማማኝነት፣ የሸርተቴ ትየባ፣ የድምፅ ትየባ፣ የእጅ ጽሁፍ እና ሌሎችም
የድምፅ ትየባ — በመሄድ ላይ ሳሉ በቀላሉ ጽሁፍን በቃል ያስጽፉ
የሸርተቴ ትየባ — ጣትዎን ከፊደል ወደ ፊደል በማንሸራተት በፍጥነት ይተይቡ
የእጅ ጽሁፍ — በቅጥልጥል እና በእትም ፊደላት ይፃፉ
የቋንቋ ድጋፍ የሚከተሉትን ያካትታል፦
አረብኛ፣ ቻይንኛ፣ ቼክኛ፣ ደች፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ግሪክኛ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ጣሊያንኛ፣ ጃፓንኛ፣ ኖርዌይኛ፣ ፖላንድኛ፣ ፖርቹጋልኛ፣ ሮማኒያኛ፣ ሩሲያኛ፣ ስፓኒሽ፣ ስዊድንኛ፣ ታይኛ፣ ቱርክኛ፣ ዩክሬንኛ እና ብዙ ተጨማሪ!
የባለሙያ ጠቃሚ ምክሮች፦
• የጠቋሚ እንቅስቃሴ፦ ጠቋሚውን ለማንቀሳቀስ ጣትዎን በክፍተት አሞሌው ላይ ያንሸራትቱ
• ቋንቋ ማከል፦
1. ወደ ቅንብሮች → ሥርዓት → ቋንቋዎች እና ግብዓት → ቁልፍ ሰሌዳ → የGoogle አውቶሞቲቭ ቁልፍ ሰሌዳ
2. ለማከል ቋንቋ ይምረጡ። የቁልፍ ሰሌዳው ላይ የሉል አዶ ይታያል
• ቋንቋዎችን መቀያየር፦ በነቁ ቋንቋዎች መካከል ለመቀያየር የሉል አዶውን መታ ያድርጉ
• ሁሉንም ቋንቋዎች መመልከት በቁልፍ ሰሌዳው ላይ የነቁ ሁሉንም ቋንቋዎች ዝርዝር ለመመልከት የሉል አዶውን በረዥሙ ይጫኑ