ትልቅ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ አዝናኝ እና ቀላል ጥያቄዎችን ይመልሱ! በደረጃዎች አልፈው ይደጉ፣ ባጆችን ይክፈቱ እና በሂደቱ ላይ ስኬቶችዎን ያጋሩ! የእርስዎ የበጎ ፈቃድ አስተዋጽዖዎች የGoogle ምርቶች በእርስዎ የዓለም ክፍል ውስጥ የተሻለ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። Google ረዳት ትርጉምን በተሻለ መልኩ እንዲረዳ፣ ለቋንቋዎ Google ትርጉምን እንዲያሻሽል እና Google ፎቶዎች ቁሶችን እንዲለይ ለማገዝ ያስተምሩት። Google በሁለቱም በአካባቢያዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሻሻል እርስዎ ማበርከት ከሚችሏቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያድጉ እና ብዝሃነት ካላቸው የአስተዋጽዖ ዓይነቶች ውስጥ እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው።
የGoogle የአስተዋጽዖ አበርካቾች ማህበረሰብን ለመቀላቀል ከእነዚህ ተግባሮች የተወሰኑትን ይሞክሩ፦
ጥያቄ መረዳት፦ የተሰጠ ጥያቄን ምን ያህል መረዳት እንደሚችሉ ይምረጡ።
የምስል ንጽጽር፦ እርስዎ በተሻለ መልኩ የወደዱት ምስል የቱ እንደሆነ ይንገሩን።
የእጅ ጽሁፍ ማረጋገጫ፦ የእጅ ጽሁፉ ከሚመለከቱት ጽሁፍ ጋር የሚዛመድ ከሆነ ይንገሩን።
የእጅ ጽሁፍ ማንበብ፦ የእጅ ጽሁፉ ምን እንደሚል መለየት የሚችሉ ከሆነ ይንገሩን።
የእጅ ጽሁፍ ንጽጽር፦ ምርጫዎን ለመምረጥ ሁለት የእጅ ጽሁፍ ቅጦችን ያነጻጽሩ።
የነጥብ ማረጋገጫ፦ የመሃል ነጥቡ ከርዕሰ ጉዳዩ አናት ላይ መሆኑን ያረጋግጡ።
የምግብ ንጽጽር፦ የሁለት የምግብ ምስሎች ባህሪያትን ያነጻጽሩ።
የኦዲዮ ልገሳ፦ የንግግር ቴክኖሎጂን ለማሻሻል ድምፅዎን ይቅዱ።
የምግብ እውነታዎች፦ አንድ የምግብ ዓይነት የተለዩ ባህሪያት ያሉት ከሆነ ይንገሩን።
የምግብ መሰየሚያ፦ አንድ ምስል ምን ምግብ እንደያዘ ይንገሩን።
የፍቺ ተመሳሳይነት፦ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም እንዳላቸው ወይም እንደሌላቸው ይፍረዱ።
የገበታ ግንዛቤ፦ ገበታዎች ለመረዳት የሚቻሉ እና እምነት የሚጣልባቸው መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን ይፍረዱ።
የሸርተቴ ትየባ፦ የሚመለከቱትን ጽሁፍ ለመተየብ ጣቶችዎን በቁልፍ ሰሌዳው ላይ ያንሸራትቱ።
የኦዲዮ ማረጋገጫ፦ አንድ አጭር የኦዲዮ ቅንጥብ ያዳምጡ እና አነባበቡ በእርስዎ ቋንቋ ተፈጥሯዊ የሚመስል መሆኑን ይወስኑ።
የምስል መግለጫ፦ የንግግር ቴክኖሎጂን ለማሻሻል ለእርስዎ የቀረቡትን ምስሎች እየገለጹ ድምፅዎን ይቅዱ።
የምስል መሰየሚያ ማረጋገጫ፦ ምስሎች በትክክል መለያ ከተሰጣቸው ይንገሩን።
የምስል ቀረጻ፦ የእርስዎን የዓለም ክፍል ፎቶዎች ይሰብስቡ እና ያጋሩ።
ትርጉም፦ ሀረጎችን እና ቃላትን ወደ የተለያዩ ቋንቋዎች ይተርጉሙ።
የትርጉም ማረጋገጫ፦ የትኛዎቹ ሀረጎች በትክክል እንደተተረጎሙ ይምረጡ።
የእጅ ጽሁፍ ለይቶ ማወቂያ፦ የእጅ ጽሁፍ ይመልከቱ እና እርስዎ የሚመለከቱትን ጽሁፍ ይተይቡ።
የስሜት ግምገማ፦ አንድ ዓረፍተ ነገር በእርስዎ ቋንቋ ውስጥ አዎንታዊ፣ አሉታዊ ወይም ገለልተኛ መሆኑን ይወስኑ።
ዘመናዊ ካሜራ፦ (Android Lollipop 5.0+ ያስፈልጋል)፦ ወደ አንድ ቁስ ይጠቁሙ እና ካሜራው ምን እንደሆነ መገመት ይችል እንደሆነ ይመልከቱ።
መልስ ባስገቡ ቁጥር የGoogle ምርቶችን ወደፊት ለሚመጡት ዓመታት የበለጠ አካታች እንዲሆኑ ያደርጋሉ። እንዲሁም ለእገዛዎ እንደ በአካባቢያዊ ስብሰባዎች ላይ ከሌሎች አስተዋጽዖ አበርካቾች ጋር መገናኘት፣ ከGoogle ሰራተኞች እና ከሌሎች አስተዋጽዖ አበርካቾች ጋር የመስመር ላይ Hangouts ልዩ ግብዣዎችን መቀበል እና በCrowdsource ማህበራዊ ሰርጦች ላይ ተለይተው መቅረብ ያሉ ጥቅሞችን ይሸለማሉ። በባቡር ላይ፣ በአውቶቡስ ፌርማታ ላይ ወይም ሰልፍ ላይ እየጠበቁ ቢሆኑም ወይም ባይሆንም Google ለአካባቢዎ ማህበረሰብ የተሻለ ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ።